ምንጭ:-http://www.danielkibret.com
click here for pdfሁለት ተማሪዎች አንድ የቤት ሥራ ተሰጣቸው፡፡ የቤት ሥራው የተማሪዎችን ችሎታ ለመፈተን በከተማ ደረጃ የተዘጋጀ የዕውቀት መለኪያ ፈተና ነበር፡፡ ይህ ፈተና በሁለት ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች ተሰጥቷቸው ነበር፡፡ አንደኛው ተማሪ አባቱ የናጠጡ ነጋዴ ሲሆኑ እናቱም አሜሪካ ተወልደው አድገው በአንድ የውጭ ድርጅት ለመሥራት ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ናቸው፡፡ እርሱም የሚማረው ‹‹አበባ የቀጠፈና አማርኛ የተናገረ ይቀጣል›› የሚል ማስታወቂያ በተለጠፈበት አንድ የግል ትምህርት ቤት ነው፡፡ ሁለተኛው ተማሪ አባቱ የቀን ሥራ በመሥራት የሚተዳደሩ እናቱም ዶሮ የሚያረቡ ናቸው፡፡ ልጁም የሚማረው ከተቋቋመ ከሦስት ዓመቱ ጀምሮ መስኮቱ ተዘግቶ በማያውቅ አንድ የመንግሥት ትምህርት ቤት ውስጥ ነው፡፡