ክፍል -2
የቀዳማዊ ምኒልክ ጉዞና የታቦተ ጽዮን መምጣት
ቀዳማዊ ምኒልክ ከአደገ በኋላ በ12 ዓመቱ ከእናቱ የተሰጠውን ለታቦተ ጽዮንና ለንጉሥ ሰሎሞን እጅ መንሻ ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም ተጓዘ፡፡ ንግሥት ሳባም ለንጉሥ ሰሎሞን “ንጉሥ ሆይ ልጄን ሙሴ የጻፋቸውን ሕግጋት ሥርዓተ ክህነት አስተምረህ ላክልኝ፡፡” የሚል መልእክት ልካ ነበር፡፡ ቀዳማዊ ምኒልክ በኢየሩሳሌም ከአባቱ ዘንድ ለሦስት ዓመት ያህል ቆይቷል፡፡ በዚሁ ዘመን መጻሕፍተ ሙሴን፣ ሕገ መንግሥትን፣ ሥርዓተ ክህነትን የዕብራይስጥን ቋንቋ ከሊቀ ካህናቱ ከሳዶቅ ተምሯል፡፡
ወደ ኢትዮጵያ ሲመለስም በፈቃደ እግዚአብሔር ታቦተ ጽዮንን ይዞልን መጥቷል፡፡ ይህች ታቦት ለ3000 ዓመታት ያህል እስከዛሬ ድረስ በኢትዮጵያ በአክሱም ትገኛለች፡፡ ንግሥት ሳባም ታቦተ ጽዮን መምጣቷን ስትሰማ ለእግዚአብሔር መስዋዕት አቀረበች፡፡ ሰዎችን መርጣ ታቦተ ጽዮንን እንዲጠብቁ አድርጋለች፡፡ የመንግሥቱን ሥልጣን በሙሉ ለቀዳማዊ ምኒልክ አስረክባ ከዚህ ዓለም በሞተ በተለየች ጊዜ በዚያው በአክሱም ተቀብራለች፡፡ ቦታውም እስከ አሁን ድረስ የንግሥት ሳባ መቃብር እየተባለ ይጠራል፡፡
በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ታሪክ ጸሐፊው አቡሳላህ “አቢሲኒያውያን በእግዚአብሔር ጣቶች አሥርቱ ቃለት የተጻፈባት፣ ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ያሉባት የቃል ኪዳኑ ታቦት አለቻቸው፡፡” በማለት ጽፎ ነበር፡፡ በዘመናችን ይህችን ታቦት ፍለጋ ያደረገው ግርሃም ሐንኮክም “The sign and the seal” በተሰኘው መጽሐፉ ይህን ገልጦታል፡፡
Wednesday, November 30, 2011
“ታቦተ ጽዮን” ፤ “ኅዳር ጽዮን“ ፤ “አክሱም ጽዮን “ ክፍል -1
የታቦተ ጽዮን መንበር -አክሱም
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከምታከብራቸው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓላት አንዱ “ኅዳር ጽዮን” ሲሆን የሚከበረውም ኅዳር 21 ቀን ነው፡፡ የበዓሉን አከባበር ፤ ጥንተ ታሪኩን፤ ንግስት ሳባ ፤ቀዳማዊ ምኒልክና ሌሎችም ተያያዥ ጉዳዮችን በተከታታይ ክፍሎች እንመለከታለን፡፡
ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን “ታቦተ ጽዮን” የፈጸመችውን ልዩ ልዩ ተአምራት ለምእመናን እያስተማረች በታላቅ ድምቀት የምታከብረው ቅዱሳት መጻሕፍትን መሠረት በማድረግ ነው፡፡ ሊቀ ነቢያት ሙሴ በደብረ ሲና አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ከጾመና ከጸለየ በኋላ ዐሥርቱ ቃላተ የተጻፈበትን ጽላት /ታቦተ ጽዮን/ ከእግዚአብሔር እጅ ተቀበለ፡፡ “ታቦተ ጽዮን” የሚለውንም ስያሜ ያገኘችው ጽዮን ተብላ በምትጠራው የእስራኤል ከተማ ስም ነው፡፡ ጽዮን ማለት ተፀወነ፡- ተጠጋ፣ ተማጠነ ማለት ነው፡፡ ክቡረ ዳዊትም ጽዮንን አምባ፣ መጠጊያ አድርጎ ብዙ ጠላቶቹን ተዋግቶ አሸንፎ ድልን ተጎናጽፏል፡፡
አጼ ፋሲል በ16ኛው ክፍለዘመን ያሰሩት ቤተክርስቲያን ከፊት ለፊት እና በጎን ሲታይ
ጽዮን የተባለችው የታላቁ የዳዊት ከተማ የተገፉና የተበደሉ ሕዝቦች ሁሉ እውነተኛ ፍርድ ለማግኘት፣ ተሰብስበው የሚሰነብቱባት ከተማ ስለነበረች፣ ጽላተ ሙሴም በዚያ ስለነበረች በርሷ ተማጽነውም ችግራቸው ሰለሚቃለል ታቦቷ “ታቦተ ጽዮን” ተብላለች፡፡
ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ በራእዩ “በሰማይ ያለችው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተከፈተች፡፡ በውስጧም ያለችው ታቦተ ሕግ ታየች፡፡” ራእይ. 11 ሚ 19 በማለት የተናገረውን ቅዱስ ኤጲፋንዮስ በመጽሐፈ አክሲማሮስ ሲተረጉመው “በሥላሴ ጸዲል በሥላሴ ብርሃን የተመላች ስመ ሥላሴ የተጻፈባት ታቦት በኢየሩሳሌም ሰማያዊት አለች፡፡
በዚህች ታቦት ላይ ከፍጥረተ ዓለም በፊት ስመ እግዝእትነ ማርያም ተጽፎባት ነበር፡፡ ቅድመ ዓለም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከመፈጠሯ በፊት በአምላክ ኅሊና ታስባ ትኖረ ነበር የሚለው መሠረቱ ይህ ነው” ብሏል፡፡ ታቦተ ጽዮን የምትኖርበትን ድንኳን ሊቀ ነቢያት ሙሴ እንዲሠራ እግዚአብሔር ነግሮታል፡፡ ሊቁ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ሲናገር “ደብተራ ኦሪትን በኢየሩሳሌም ሰማያዊት አርአያና ምሳሌ እንዲሠራ እግዚአብሔር አሳይቶታል፡፡ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ሁለንተናዋ ከብርሃን የተሠራች ናት፡፡ የኢየሩሳሌም ሰማያዊት ቅርጽም ደብተራ ኦሪትን ትመስላለች፡፡” ይላል፡፡ ሕዝቡም ከፈጣሪያቸው ጋር ቃል ኪዳን ገብተው በታቦተ ጽዮን አማካኝነት ሲያመሰግኑ ኑረዋል፡፡ ታቦተ ጽዮን እግዚአብሔርን ለሚያምኑ፣ ሕጉን ትእዛዙን ለሚፈጽሙ ሰዎች ሁሉ ልዩ ልዩ ተአምራትን እንደፈጸመች ከቅዱስ መጽሐፈ እንረዳለን፡፡ እስራኤላውያን ሕጉን ሲጠብቁ ትእዛዙን ሲፈጽሙ እግዚአብሔር በታቦተ ጽዮን እያደረ ይረዳቸውና ጠላቶቻቸውንም ድል ያደርጉ ነበር፡፡ ሕጉን ሲያፈርሱ ደግሞ በጠላቶቻቸው ይሸነፉ ነበር፡፡ አጼ ኃይለሥላሴ ያሰሩት ቤተክርስቲያን - አክሱም በዚያ ዘመን ኤሊ የሚባል ሊቀ ካህናት ነበር፡፡ አፍኒንና ፊንሐስ የሚባሉ ሁለት ልጆች ነበሩት፡፡ እድሜውም 98 ዓመት ነበር፡፡ አፍኒንና ፊንሐስ የአባታቸውን ምክር አቃልለው የማይገባ ኃጢአት ሠርተው አምላካቸው እግዚአብሔርን አሳዘኑ በራሳቸው ፈቃድ ተጉዘው ሕገ እግዚአብሔርን ጣሱ፡፡ በሕዝቡም ላይ የሚያደርሱት በደል እየጨመረ ሔደ፡፡ አፍኒንና ፈንሐስ እግዚአብሔር በኃጢአታቸው ምክንያት በረድኤት ስለተለያቸው ፍልስጥኤማውያን በጠላትነት ተነሡባቸው፡፡ እስራኤላውያን ከኤሊ ልጆቸ ጋር ሆነው በአንድነት ታቦተ ጽዮንን ይዘው ለጦርነት ወደ ፍልስጥኤም ዘመቱ፡፡ ጦርነትም ገጠሙ ታላቅ ግድያም ሆነ፡፡ በጦርነቱ አፍኒንና ፊንሐስ ሞቱ፡፡ ታቦተ ጽዮንም በኤሎፍላውያን እጅ ተማረከች፡፡ ሕዝቡም በጦርነት አለቁ፡፡ ከጦርነቱ ያመለጠ አንድ ሰው ወደ ኤሊ ሄዶ እስራኤላውያን ተሸንፈው መሸሻቸውን፡ ሁለቱ ልጆቹ አፍኒንና ፊንሐስ መሞታቸውን ታቦተ ጽዮንም መማረኳን ነገረው፡፡ ኤሎፍላውያንም ታቦተ ጽዮንን ማርከው ከወሰዷት በኋላ ዳጎን ከተባለው ጣዖታቸው በታች አስቀመጧት፡፡ በማግስቱ የዳጎን አገልጋዮች መጥተው ቢያዩአት ፣ ዳጎን ከእግዚአብሔር ታቦት ፊት በግንባሩ ተደፍቶ አገኙት፡፡ አንስተው አቁመውት ሔዱና በማግስቱ መጥተው ቢያዩት በግንባሩ ወድቆ እጆቹ ተለያይተው ጣቶቹም ተቆራርጠው ደቀው በወለሉ ላይ ተበታትነው ነበር፡፡
በዚህች ታቦት ላይ ከፍጥረተ ዓለም በፊት ስመ እግዝእትነ ማርያም ተጽፎባት ነበር፡፡ ቅድመ ዓለም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከመፈጠሯ በፊት በአምላክ ኅሊና ታስባ ትኖረ ነበር የሚለው መሠረቱ ይህ ነው” ብሏል፡፡ ታቦተ ጽዮን የምትኖርበትን ድንኳን ሊቀ ነቢያት ሙሴ እንዲሠራ እግዚአብሔር ነግሮታል፡፡ ሊቁ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ሲናገር “ደብተራ ኦሪትን በኢየሩሳሌም ሰማያዊት አርአያና ምሳሌ እንዲሠራ እግዚአብሔር አሳይቶታል፡፡ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ሁለንተናዋ ከብርሃን የተሠራች ናት፡፡ የኢየሩሳሌም ሰማያዊት ቅርጽም ደብተራ ኦሪትን ትመስላለች፡፡” ይላል፡፡ ሕዝቡም ከፈጣሪያቸው ጋር ቃል ኪዳን ገብተው በታቦተ ጽዮን አማካኝነት ሲያመሰግኑ ኑረዋል፡፡ ታቦተ ጽዮን እግዚአብሔርን ለሚያምኑ፣ ሕጉን ትእዛዙን ለሚፈጽሙ ሰዎች ሁሉ ልዩ ልዩ ተአምራትን እንደፈጸመች ከቅዱስ መጽሐፈ እንረዳለን፡፡ እስራኤላውያን ሕጉን ሲጠብቁ ትእዛዙን ሲፈጽሙ እግዚአብሔር በታቦተ ጽዮን እያደረ ይረዳቸውና ጠላቶቻቸውንም ድል ያደርጉ ነበር፡፡ ሕጉን ሲያፈርሱ ደግሞ በጠላቶቻቸው ይሸነፉ ነበር፡፡ አጼ ኃይለሥላሴ ያሰሩት ቤተክርስቲያን - አክሱም በዚያ ዘመን ኤሊ የሚባል ሊቀ ካህናት ነበር፡፡ አፍኒንና ፊንሐስ የሚባሉ ሁለት ልጆች ነበሩት፡፡ እድሜውም 98 ዓመት ነበር፡፡ አፍኒንና ፊንሐስ የአባታቸውን ምክር አቃልለው የማይገባ ኃጢአት ሠርተው አምላካቸው እግዚአብሔርን አሳዘኑ በራሳቸው ፈቃድ ተጉዘው ሕገ እግዚአብሔርን ጣሱ፡፡ በሕዝቡም ላይ የሚያደርሱት በደል እየጨመረ ሔደ፡፡ አፍኒንና ፈንሐስ እግዚአብሔር በኃጢአታቸው ምክንያት በረድኤት ስለተለያቸው ፍልስጥኤማውያን በጠላትነት ተነሡባቸው፡፡ እስራኤላውያን ከኤሊ ልጆቸ ጋር ሆነው በአንድነት ታቦተ ጽዮንን ይዘው ለጦርነት ወደ ፍልስጥኤም ዘመቱ፡፡ ጦርነትም ገጠሙ ታላቅ ግድያም ሆነ፡፡ በጦርነቱ አፍኒንና ፊንሐስ ሞቱ፡፡ ታቦተ ጽዮንም በኤሎፍላውያን እጅ ተማረከች፡፡ ሕዝቡም በጦርነት አለቁ፡፡ ከጦርነቱ ያመለጠ አንድ ሰው ወደ ኤሊ ሄዶ እስራኤላውያን ተሸንፈው መሸሻቸውን፡ ሁለቱ ልጆቹ አፍኒንና ፊንሐስ መሞታቸውን ታቦተ ጽዮንም መማረኳን ነገረው፡፡ ኤሎፍላውያንም ታቦተ ጽዮንን ማርከው ከወሰዷት በኋላ ዳጎን ከተባለው ጣዖታቸው በታች አስቀመጧት፡፡ በማግስቱ የዳጎን አገልጋዮች መጥተው ቢያዩአት ፣ ዳጎን ከእግዚአብሔር ታቦት ፊት በግንባሩ ተደፍቶ አገኙት፡፡ አንስተው አቁመውት ሔዱና በማግስቱ መጥተው ቢያዩት በግንባሩ ወድቆ እጆቹ ተለያይተው ጣቶቹም ተቆራርጠው ደቀው በወለሉ ላይ ተበታትነው ነበር፡፡
Saturday, November 12, 2011
«በህልምም ተረድቶ ወደገሊላ ሀገር ሄደ፤....... ናዝሬት ወደምትባልም ከተማ መጥቶ ኖረ»
ሕዳር 6 ቀን እመቤታችን ጌታን ይዛ ከግብጽ /ከስደት/ ወደ ኢየሩሳሌም መመለሷ ይታሰባል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ
አፈወርቅ ቀጥሎ ካለው የማቴዎስ ወንጌል ምንባብ በመነሳት ይህንን አስመልክቶ በማቴዎስ ወንጌል ትርጓሜው ላይ
ያስተማረውን ትምህርት እናቀርባለን፡፡
«ሄሮድስም ከሞተ በኋላ እነሆ የጌታ መልአክ በግብጽ ለዮሴፍ በህልም ታይቶ የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና
ተነሳ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ እስራኤል ሀገር ሂድ አለው፡፡ ዮሴፍም ተነስቶ ሕፃኑንና እናቱን በመያዝ ወደ
እስራኤል ምድር ተመለሰ፤ ነገር ግን አርኬላዎስ በአባቱ ፈንታ በይሁዳ መንገሱን በሰማ ጊዜ ወደዚያ መሄድ ፈራ፤
በህልምም ተረድቶ ወደገሊላ ሀገር ሄደ፤ በነቢያት ናዝራዊ ይባላል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ናዝሬት ወደምትባል ከተማ
መጥቶ ኖረ» /ማቴ. 2-19-23/፡፡
ዮሴፍ የሕፃናቱ ገዳይ መሞቱን ሰምቶ ከስደት ተመልሶ ወደ ሀገሩ ተመልሶ መጣ፡፡ ነገር ግን ገና እግሩ ሀገሩን እንደረገጠ በድጋሚ የቀደመውን አደጋ ቅሪት /ተረፍ/ አገኘ፤ የክፉው ገዢ ልጅ ንጉስ ሆኗል፡፡
ሄሮድስ በንጉስነት የሚመራትን ሀገር /እስራኤልን/ ለሦስት ከፋፍሎ ሦስቱ ልጆቹ በእርሱ ስር ሆነው በሀገረ ገዢነት እንዲመሯት አድርጎ ነበር፡፡ እርሱ ከሞተ በኋላ ቆይተው እነዚህ ልጆቹ መንግስቱን ለሦስት ተካፍለውታል፡፡ የበላይ ንጉስም አልነበረም፡፡ አሁን ግን ሄሮድስ ገና መሞቱ ስለሆነ መንግስቱ ገና አልተከፋፈለምና ልጁ አርኬላዎስ ለጥቂቱ ለጊዜው መንግስቱን ተቀብሎ ንጉስ ሆነ፡፡
ዮሴፍ በአርኬላዎስ ምክንያት ይሁዳ መቀመጥ ከፈራ /ቤተልሔም የምትገኘው በይሁዳ ነው/ በወንድሙ በሄሮድስ አንቲጳስ ምክንያት ናዝሬት መቀመጥን ለምን አልፈራም? /ናዝሬት የምትገኘው የሄሮድስ አርኬላዎስ ወንድም ሄሮድስ በአንቲጳስ በሚገዛት በገሊላ ነው/ ይህ በቂ ምክንያት አይሆንም?
ዮሴፍ የሕፃናቱ ገዳይ መሞቱን ሰምቶ ከስደት ተመልሶ ወደ ሀገሩ ተመልሶ መጣ፡፡ ነገር ግን ገና እግሩ ሀገሩን እንደረገጠ በድጋሚ የቀደመውን አደጋ ቅሪት /ተረፍ/ አገኘ፤ የክፉው ገዢ ልጅ ንጉስ ሆኗል፡፡
ሄሮድስ በንጉስነት የሚመራትን ሀገር /እስራኤልን/ ለሦስት ከፋፍሎ ሦስቱ ልጆቹ በእርሱ ስር ሆነው በሀገረ ገዢነት እንዲመሯት አድርጎ ነበር፡፡ እርሱ ከሞተ በኋላ ቆይተው እነዚህ ልጆቹ መንግስቱን ለሦስት ተካፍለውታል፡፡ የበላይ ንጉስም አልነበረም፡፡ አሁን ግን ሄሮድስ ገና መሞቱ ስለሆነ መንግስቱ ገና አልተከፋፈለምና ልጁ አርኬላዎስ ለጥቂቱ ለጊዜው መንግስቱን ተቀብሎ ንጉስ ሆነ፡፡
ዮሴፍ በአርኬላዎስ ምክንያት ይሁዳ መቀመጥ ከፈራ /ቤተልሔም የምትገኘው በይሁዳ ነው/ በወንድሙ በሄሮድስ አንቲጳስ ምክንያት ናዝሬት መቀመጥን ለምን አልፈራም? /ናዝሬት የምትገኘው የሄሮድስ አርኬላዎስ ወንድም ሄሮድስ በአንቲጳስ በሚገዛት በገሊላ ነው/ ይህ በቂ ምክንያት አይሆንም?
Tuesday, October 18, 2011
የኮፕቲክ ኦርቶዶክሶች ጉዳይ እኛን አይመለከተንም እንዴ?
ቀደምት የኮፕቶች ፈተና
ምንጭ :-andadirgen.- ለተቃውሞ በወጡት ኦርቶዶክሶች ላይ በጎማ ታንክ ሄደውባቸዋል
- «እንደ አባቶቻችሁ ለእግዚአብሔር ብቻ ስትሉ አገልግሉ፡፡ የናንተ አባቶች ለእግዚአብሔር ብቻ ሲሉ የሚያገለግሉ ነበሩ» አቡነ ሺኖዳ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አማኞች ያስተላለፉት መልእክት
- በመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ ይሰሩ የነበሩት ክርስትያኖች ጥፋት ክርስትያን በመሆናቸው ብቻ ይባረሩ ነበር፡፡
- ገደብ የለሽ ግብርና የነፍስ ወከፍ ታክስ እንዲከፍሉ ይገደዱ ነበር፡፡
- አንድ ፓትርያርክ ሞቶ ሌላ ለመተካት ከገዥዎች ፍቃድ ለመጠየቅ ከፍተኛ ገንዘብ ይሰጥ ነበር፡፡
- በእስክንድርያ ቤተክርስትያን ፓትርያርኮች ላይ እስራት እና ስቃይ ገዥዎቹ ያደርሱባቸው ነበር፡፡
- በመስቀል ጦርነት ጊዜ እስላሞቹ በተዋህዶዎችና በምዕራብ መለካውያን መካከል የተፈጠረውን ስር የሰደደ ቅራኔ ግንዛቤ ውስጥ ሳያስገቡ ክርስትያን በመሆናቸው ብቻ በተዋህዶዎች ለመስቀል ጦረኞች(ካቶሊኮች) ያግዛሉ ብለው በመጠራጠር በዓይነ መዓት ይመለከቷቸው ነበር፡፡
- አብያተ ክርስትያናቱን ከነሀብታቸው ያለ የሌለ ሀብታቸው ተሟጦ የተወረሱበት ጊዜ ነበር፡፡
- የሱኒ እስልምና እምነት ተከታይ የነበረው ሳላዲን የተባለው የግብፅ ገዥ የአስተዳደር ስራውን እንደጀመረ ክርስትያኖችን ከተለያዩ የስራ ቦታዎች ከማባረሩ በተጨማሪ የውርደት ምልክት የሆነው ከጥቁር ልብስ በስተቀር ነጭና በተለያዩ ህብረ ቀለማት ያጌጡ ልብሶችን እንዳይለብሱ ፤ ፈረስ እንዳይጋልቡ ፤ ከፍ ያለ መቀጫ ገንዘብ ለመንግስት እንዲከፍሉ በማዘዙ ክርስትያኖቹ በግፍ የተጣለባቸውን ገንዘብ ለመክፈል ያለ የሌለ ሐብታቸውን ሸጠዋል፡፡ ርስታቸውንም ለእስላሞች እንዲሸጡ በመገደዳቸው ርዕስት አልባ ሆነዋል፡፡ የመከራው የግፉን ቀንበር መሸከም ያልቻሉት አንዳንድ ክርስትያኖችም በነፃነት ለመኖርና ባለመብት ለመሆን የእስልምና እምነት መቀበል የግድ በመሆኑ ሳይወዱ በግድ ሰልመዋል

ኮፕቶችና የጊዜው ፈተናቸው
በግብፅ ውስጥ የሚኖሩ የክርስትያኖች ቁጥር የህዝቡን 10 በመቶ በላይ ሲሆን በቁጥም ከ8ሚሊየን ይልቃል በሀገራቸው ፤ እትብታው በተቀበረበት ቦታ ላይ የሁለተኛ ዜግነት ተደርገው ነው የሚወሰዱት በአሁኑ
ጊዜ ኮፕቶች የማይሸከሙትን ጫና በእስላማውያኑ እየደረሰባቸው ይገኛል፡፡ ቤተክርስትያን መስራት አይችሉም ፤ ተገደው
ከሙስሊሞች ጋር እንዲጋቡ ያደርጓችዋል ፤ አንድ ሰው ከክርስትና ወደ እስልምና ተገዶ እንዲቀይር በማድረግ
በመፅሄቶቻቸው በጋዜጦቻቸው ሲያወጡ ፤ አንድ ሰው ግን አምኖ ከእስልምና ወደ ክርስትና እምነት ቢቀይር የሚገጥመው
ሞት ብቻ በመሆኑ ዝምታውን መርጠው ሀገር ቀይረው ይኖራሉ እንጂ ባደጉበት አካባቢ የመኖር ነፃነታቸው የተገፈፈ ነው፡፡
የሙባረክ መንግስት በስልጣን ላይ እያለ የተቃውሞ ድምፅ በካይሮ ምድር በጣሂር አደባባይ ሳይሰማ
በ2011 አዲስ ዓመት የመጀመሪያው ቀን ላይ የኮፕት ኦርቶዶክሶች የጌታችንና የመድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ
ልደቱን በቤተክርስትያናቸው ላይ አክብረው ወደ ቤታቸው ለመሄድ ከቤተ መቅደስ ሲወጡ መንግስት በቂ ፖሊስ ባለመመደቡ
አክራሪ ሙስሊሞች ሶስት መኪና ላይ ባጠመዱት ቦምብ ምክንያት አካባቢውን ዋይታና ለቅሶ እንዲነግስበት ያደረጉ ሲሆን ‹‹በየአደባባዮቻቸው እንባ እጅግ እያፈሰሱ ሁሉም አልቅሰዋል።›› ትንቢተ ኢሳይያስ 15፤3 የክርስትያኖች ደም ያለአግባብ እንደ ውሀ የፈሰሰበት ፤ የ33 የኮፕት ክርስትያኖች ህይወት ያለፈበት ጊዜ ነበር፡፡ ‹‹ጌታ እግዚአብሔርም ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል›› ትንቢተ ኢሳይያስ 25፤8 ብሎ ኢሳያስ እንደተናገረው እግዚአብሔር እንባቸውን አንድ ቀን እንደሚያብስላቸው በመተማመን ከነፈተናቸው በእምነታቸው ፀንተው እየኖሩ ይገኛሉ::
በቅርብ ጊዜያት በግብፃውያን ክርስቲያኖች ላይ አደጋዎች እየበዙ ስለመጡ ሰዎች ወደ ውስጥ ሲገቡ በኤልክትሪክ መፈተሸ መሳሪያ እየተፈተሹ ነው፡፡ በየትኛውም የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ስትገቡ መፈተሸ ግድ ነው ፡፡ ይህ የሚያሳየን ምን ያህል ፈተና ላይ እንዳሉ፤ የተሸከሙት ቀንበር ከባድ መሆኑን ጭምር ነው፡፡
በአክራሪ ሙስሊሞች በተለያዩ የግብጽ አካባቢዎች
በክርስቲያኖች ላይ የሚፈጸሙትን ጭፍጨፋዎችና ግድያዎች እንዲሁም ወጣት ክርስቲያን ሴቶችን በግድ እያገቡ ማስለም
እና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ረገጣዎችን በማስመልከት በ1971 ኖቬምበር 14 ቀን በመንበረማርቆስ የተቀመጡት ፖፕ
ሺኖዳ እንዲህ ብለው ነበር
“ስሙ ወንድሞቼ፤ ልናገረው የምሻው ብዙ ነገር በአእምሮዬ ነበረኝ። በልቤም ውስጥ ከዚያ የሚበልጥ ብዙ ነገር አለ። ይሁን እንጂ ዝም ማለትን እመርጣለሁ። እኔ ዝም ማለትን የመረጥኹት (በምትኩ) እግዚአብሔር እንዲናገር ስለምፈልግ ነው። እመኑ፤ ዝምታችን ከመናገር በላይ ገላጭ ሊሆን ይችላል። እግዚአብሔር ደግሞ ዝምታችንን እያዳመጠ ነው። እግዚአብሔር ዝምታችንን ይሰማል። የዝምታችንን ትርጉምና እየደረሰብን ያለውን መከራም ያውቃል። መከራ እየተቀበልንበት ስላለው ጉዳይ ነገራችንና ችግራችንን ሁሉ ለእግዚአብሔር አሳልፈን እንሰጣለን። በእጆቹም ላይ እንተወዋለን። እናም ‘ያንተ ፈቃድ ይሁን/ ወይኩን ፈቃድከ’ እንላለን። (ጌታ ሆይ) ‘ይህንን ችግር መፍታት ከፈለግኽ ፈቃድህ ይሁን፣ የመከራን መስቀል እንድንሸከም ከፈቀድክም… (ካሉ በኋላ እንባቸውን እያፈሰሱ አለቀሱ) “…ችግራችንን ለእግዚአብሔር እንስጥ/ እንተው ያልኩበት ምክንያት እግዚአብሔር ሁሉን የሚገዛ/ የሚቆጣጠር ስለሆነ ነው። እርሱ ሁሉን ያያል። ሁሉንም ነገር ይሰማል። ሁሉንም ነገር ያውቃል።” በማለት ነበር
በቅርቡ በኮፕት ኦርቶዶክሶች የሀገሪቱ የዜና ማሰራጫ ጋር ሄደው ባሰሙት ሰላማዊ ድምጽ ግጭት የተፈጠረ ሲሆን በግጭቱ ፖሊሶች ህግ ከሚፈቅደው ውጪ ለተቃውሞ በወጡት ኦርቶዶክሶች ላይ በጎማ ታንክ ሄደውባቸዋል ፤የአለም መንግስታት የተለያዩ የእምነት ተቋማት የ26 ሰዎችን ነፍስ የቀጠፈውን ፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ክርስትያኖች ከፍተኛ የአካል ጉዳት የደረሰበትን ሁኔታ ግጭት ሲያወግዙ በዘጠኝ ወር ጊዜ ውስጥ ከ80 በላይ ክርስትያኖች እንደተገደሉ ከቢቢሲ ዘገባ ለመረዳት ችለናል፡፡
ኮፕቶችና እኛ
አፄ ኃ/ስላሴ ከግብፅ ፓትርያርክ ጋር
ከ4መቶ ዓመታ በፊት ታሪክ እንደሚያስረዳን በአፄ ዳዊት ዘመነ መንግስት ኮፕቶች እንደ አሁኑ ጊዜ ስቃዩ በዝቶባቸው የክርስትያን መንግስት ለነበራት ለኢትዮጵያ መልዕክት ልከው ነበር ፡፡ በግብጽ
ያሉ ሙስሊሞች እየበዙ ኃይላቸው እየጠነከረ ሲሔድ በእስክንድርያ የሚኖሩትን ክርስቲያኖች ላይ ሥቃይ ያጸኑባቸው
ጀመር ክርስቲያኖቹም አንድ ሆነው መክረው ለኢትዮጵያዊ ዓፄ ዳዊት እንዲህ የሚል መልዕክት ላኩ “ንጉሥ ሆይ! በዚህ በግብጽ ያሉ እስላሞች መከራ አጽንተውብናልና ኃይልህን አንሥተህ አስታግሥልን ብለው ጠየቁት”
ዳግማዊ ዓፄ ዳዊትም ለመንፈሳዊ ኃይማኖት ቀንተው የክርስቶስ ፍቅር አስገድዶአቸው ፳ ሽህ ሠራዊት አስከትለው ወደ
ግብፅ ዘመቱ በዚህ ጊዜ በግብፅ ያሉ ኃያላን ፈሩ ተሸበሩ ንጉሡ ዳግማዊ ዳዊትም እንዲህ የሚል መልዕክትና
ማስጠንቀቂያ ለሙስሊሞቹ ላኩ ‹‹በተፈጥሮ ወንድሞቻችሁ ከሆኑት ክርስቲያኖች ጋር ካልታረቃችሁ ሀገራችሁን መጥቼ አጠፋዋለሁ›› ፡፡የንጉሡ መልዕክት ለሙስሊሞቹ እንደደረሳቸው ፈርተው እንደ ጥንቱ በየሃይማኖታቸው ፀንተው በሰላም እንዲኖሩ ከክርስቲያን ወንድሞቻቸው ጋር ታረቁ፡፡
መታረቃቸውን
ዳግማዊ ዳዊት ሰሙ በዚህም ጉዳይ ንጉሡ በጣም ደስ አላቸው እገዚአብሔርንም አመሰገኑ በግብፅ የሚኖሩ ክርስቲያኖችም
ከ፲፪ ሺህ ወቄት ወርቅ ጋር ደስታቸውን ለኢትዮጵያዊው ንጉሥ ለዳግማዊ ዳዊት በደብዳቤ አድርገው ላኩላቸው ንጉሡም
የደስታውን ደብዳቤ ተመልከተው ደስ ኣላቸው ፤ ወርቁን ግን መልሰው በመላክ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ፃፉ ‹‹በግብፅ
የምትኖሩ የክርስቶስ ተከታዮች ሆይ እንኳን ደስ አላችሁ የላካችሁልኝን ፲፪ ሺህ ወቄት ወርቅ መልሼ ልኬላችኋለሁ
የእኔ ዓላማ ወርቅ ፍለጋ አይደለም የክርስቶስ ፍቅር አስገድዶኝ ነው በተቻለኝ መጠን ችግራችሁን ሁሉ
አስወገድኩላችሁ …..››
ይህ
የሚያሳየን ቀደምት አባቶቻችን በክርስትና ላይ የሚደረግ ጥቃት ራስ ላይ እንደደረሰ አድርገው ቆጥረው በቻሉት መጠን
ጦርም ሰብቀው ይሁን በሌላ መንገድ መፍትሄ እንደሚሹላቻ ነበር:: አሁን ግን ጊዜው የተገላቢጦሽ ሆነና
የክርስትያኖች ደም ሲፈስ በአይናችን እያየን በጆሯችን እየሰማን እንዳላየን ማለፉን መርጠናል፡፡ የኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ሲኖዶስ እንኳን ኦፊሺያል የሆነ ደብዳቤ ለኮፕት ክርስትኖች የሀዘናቸው ተካፋይ መሆኑን
እግዚሐብሔር ባጋጠማቸው ፈተና እንዲያፅናናቸው ደብዳቤ ለመፃፍ አለመቻላችንን ሳስበው በጣም ይገርመኛል:: እንደ
አባቶቻችን ጦር ሰብቀን ያሉበትን ጫና እናስለቅቃቸው አላልኩም፡፡ ባይሆን አንድ ነጠላ ገፅ መልዕክት ፅፈን
ብናፅናናቸው መልካም መስሎ ስለታየኝ ነው:: አሁን ካሉት አባቶቻችንስ ይህን ሀሳብ የሚያነሳ አባት ጠፍቶ ነው?
በመሰረቱ የራሳችንም ችግር አላስተነፍስ ብሎናል ይህን አውቃለሁ ፤ ችግሮቻችን እግር አውጥተው መሄድ ከጀመሩ
ሰንበትበት ብለዋል ፡፡ ቤተክርስትያችን የእሷ ባልሆኑት ሰዎች እናድስሽ ፤ መታደስ አለባት በሚሉ ሰዎች ብትከበብ
እንኳን ሌላ ቦታ የሚደረግ ኢ-ክርስትያናዊ የሆነ ምግባርን ኦፊሺያል በሆነ መልኩ መቃወም መቻል አለብን የሚል እምነት ስላለኝ ነው፡፡
እርስዎ ምን ይላሉ?
‹‹እግዚአብሔር ለኮፕት ኦርቶዶክሶች መፅናናቱን ይስጣቸው››
ጥቂት ምንጭ
- ከመላኩ አዘዘው ድህረ ገፅ (ግማደ መስቀሉ)
- አናቅፅ ሲኦል (ከብርሀኑ ጎበና)
Monday, October 3, 2011
መርዙ
ምንጭ፡- www.danielkibret.com እነሆ ሁለት ባል እና ሚስቶች መኖራቸው ተነገረ፡፡ ግን ፈጽሞ ሊስማሙ አልቻሉም ተባለ፡፡ ቤታቸው የትዳር ቤት ሳይሆን አፍጋኒስታን ይመስል ነበር፡፡ አንዳንድ ጊዜ እንዲያውም ለምን ሊጋቡ እንደቻሉ ሁለቱንም ያስገርማቸዋል፡፡ አንድ ደራሲ Men from Mars and women from Venus የሚል መጽሐፍ ጽፏል፡፡ እንደተፈጥሯቸው እና ጠባያቸው ቢሆን ኖሮ ወንድ እና ሴት ተጋብተው መኖር የማይችሉ ፍጡራን ነበሩ ነው ጠቅላላ ሃሳቡ፡፡ የትዳር የዘለቄታ ፎርሙላም ይህንን እውነታ ከመረዳት ይመነጫል ባይ ነው፡፡
ታድያ እነዚህኞቹ ከዚህም የባሱ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ እና ጣልያን፣ እንግሊዝ እና አርጀንቲና፣ አሜሪካ እና ቬትናም፣ ይመስላሉ፡፡
አንዳቸው የሚናገሩት ለሌላቸው አይጥምም፡፡ እንዋደዳለን ብለው ሳይሆን እንበሻሸቃለን ብለው የተጋቡ ይመስላሉ፡፡ ሁለት ተቀዋዋሚ ፓርቲዎች አንድ መንግሥት መሥርተው እርስ በርስ መከራ የሚያዩበት ሀገር ሆኗል ቤታቸው፡፡ «ትዳር ማለት ከውጭ ያሉት እንግባ እንገባ፣ ከውስጥ ያሉት እንውጣ እንውጣ የሚሉበት ነው» የተባለው የተፈጸመው በእነርሱ ነው፡፡
በቤታቸው ቀስ ብሎ የሚናገር የለም፡፡ ባልም ይጮኻል፣ ሚስትም ትጮኻለች፤ እነርሱንም ተከትትሎ ቤቱ ራሱ ይጮኻል፡፡ የሚገርመው ነገር በሩ ሲከፈት ይጮኻል፤ ቴሌቭዥኑ ይጮኻል፤ ጠረጲዛው ሲሳብ ይጮኻል፤ ወንበሩ ሲጎተት ይጮኻል፤ ሁሉም ይጮኻል፡፡
ከአማርኛ ድምፆችች ሁሉ «ዬ» የምትባለው ድምፅ እዚህ ቤት እንዳትደርስ ተከልክላለች፡፡ «እንትናዬ» እየተባለ ሲጠራ ሰማሁ የሚል የለም፡፡ «እ አንተ፣ እ አንቺ፣ ስማ፣ ስሚ» ቤቱ የወታደር ካምፕ ነው የሚመስለው፡፡
እናም ሁለቱም መረራቸው፡፡ መፋታት አሰቡ፤ ግን ፍርድ ቤት ምን እንደሚወስን አይታወቅም፡፡ ለአንዱ አብልጦ ለሌላውም አሳንሶ ቢወስን ሞት መስሎ ተሰማቸው፡፡ ይኼ በቤታቸው ገብቶ የሚያነታርካቸው ሰይጣን ለሁለቱም በአንድ ጊዜ አንድ ክፉ ነገር አመለከታቸው፡፡ አንዱ ሌላኛውን በመርዝ ለመግደል፡፡ አሰቡ ሁለቱም፡፡ እናም ምናልባት መፍትሔ ይሰጠናል ብለው ወደሚያስቡበት አንድ ዐዋቂ ዘንድ ለመሄድ በየግላቸው ወሰኑ፡፡
መጀመርያ ባል ከሚስቱ ተደብቆ ዓርብ ዕለት ወደ ዐዋቂው ቤት ሄደ፡፡ እዚያም ደርሶ ችግሩን ሁሉ ነገረው፡፡ «እኔ ከሚስቴ ጋር መነታረክ ሰለቸኝ፤ አንድ ቀን እንደ ሰው ጥሩ ነገር ሳንነጋገር ይኼው አምስት ዓመት ሆነን፡፡ ነጋ ጠባ ጠብ ነው፡፡ አሁን መረረኝ፡፡ እርሷ ከግራ ጎኔ ሳይሆን ከምላሴ ነው የተፈጠረችው፡፡ የመጣሁት እርሷን ጸጥ አድርጎ የሚገድል መርዝ እንድትሰጠኝ ነው» አለው፡፡ ዐዋቂውም በሃሳቡ ተስማማ፡፡ «ነገር ግን» አለው ዐዋቂው «ሚስትህን በአንድ ቀን በመርዝ ብትገድላት ተጠርጥረህ ትያዛለህ፡፡ ስለዚህ ቀስ በቀስ የሚገድል መርዝ ልስጥህ» አለው፡፡ ባልም ተስማማ፡፡ «ይኼ መርዝ በምግብ፣ በመጠጥ፣ በአልጋ ላይ፣ በወንበር ላይ የሚደረግ ነው፡፡ ሚስትህ ጠርጣራ ናት፡፡ ልትደርስብህ ትችላለች፡፡ ጎረቤቶችህም እንደምትጣሉ ያውቃሉ፡፡ አንድ ነገር ብትሆን ይጠረጥሩሃል፡፡
ስለዚህ ከዛሬ ጀምሮ ጠባይህን ቀይር፡፡ እያቆላመጥክ በስሟ ጥራት፡፡ አልጋዋን አንጠፍላት፣ ምግቧን ሥራላት፤ ከውጭ ስትመጣ ስጦታ አምጣላት፤ ሻሂ አፍላላት፤ ራት ጋብዛት፤ ልብሷን ተኩስላት፤ እንዴው በአጠቃላይ ተንከባከባት፡፡ ነገር ግነ ምግብ ስታበላት በምግብ ላይ፣ መጠጥ ስታጠጣት በመጠጡ ላይ፣ ልብሷን ስትተኩስ በልብሷ ላይ፣ አልጋ ስታነጥፍ በአልጋው ራስጌ በኩል ይህንን መድኃኒት ቀስ አድርገህ በትንበት፡፡ ቀስ በቀስ ይገድላታል፡፡ አንተም ትገላገላለህ» አለው፡፡
ባልዬው ተደሰተ፡፡ ያላሰበውን የመፍትሔ ሃሳብ ዐዋቂው በማምጣቱ ዘሎ አቀፈው፡፡ በኪሱ የነበረውን ገንዘብም እንዳለ አወጣ፡፡ ያን ጊዜ ዐዋቂው «አሁን አትከፍልም፤ መድኃኒቱ ሠርቶ ሚስትህ ከሞተች በኋላ ትከፍላለህ፤ አንድ ነገር ግን ጠብቅ፡፡ ሚስትህ ምናልባት ጠባይዋን ለትቀይር ትችላለች፤ ያን ጊዜ መድኃኒቱ እየሠራ መሆኑን በዚህ ታረጋግጣለህ» አለው፡፡ እየፈነጠዘ መድኃኒቱን ቋጠሮ ወደ ቤቱ ሄደ፡፡
በማግሥቱ ደግሞ ሚስቱ ተደብቃ መጣች፡፡ «ባሌ ሊገድለኝ ነው፡፡ እኔኮ ባል ሳይሆን ሙቀጫ ነው ያገባሁት፡፡ ሥራው መጨቅጨቅ ብቻ፡፡ አሁን የመጣሁት ከዚህ ሰው ጋር ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ እንድትለየኝ ነው፡፡ መርዝ የለህም ወይ» አለቺው፡፡ «ሞልቷል» አላት ዐዋቂው በፈገግታ፡፡ «የፈለግከውን ያህል ልክፈለህ ስጠኝ» አለቺው፡፡
ወደ ጓዳ ገባና በጨርቅ የተቋጠረ ነገር ይዞላት መጣ፡፡ «እይውልሽ ይሄ መርዝ ነው፤ ግን በአንድ ቀን አይገድልም» አላት፡፡ ተናደደች፡፡ «እኔ ኳ ኮርኳ የሚያደርገውን ነው የምፈልገው» አለቺው፡፡ «እርሱማ አደጋ አለው፡፡ ጤነኛ የነበረ ሰው በድንገት ሲሞት መመርመሩ፣ መጠርጠሩም አይቀር፡፡ ለእኔም ትተርፊኛለሽ» አላት፡፡ አሰብ አደረገቺና «ታድያ ምን ይሻላል?» አለቺው፡፡ «ቀስ በቀስ የሚገድል ይሻልሻል፤ እየታመመ ስለሚሞት ሰው አያውቅብሽም» አላት፡፡ ተስማማች፡፡
«አወሳሰዱ ጥንቃቄ ይፈልጋል፡፡ በምግብ፣ በመጠጥ፣ በአልጋ፣ በወንበር፣ በልብስ፣ ነው የሚሰጠው፡፡ መጀመርያ ጠባይሺን ቀይሪ፡፡ ያለበለዚያ እሺ ብሎ አይወስድልሺም፡፡ የወደድሺው ምሰዪ፡፡ እቀፊው፣ ሳሚው፣ እጅ የሚያስቆረጥመውን ምግብ ሥሪለት፤ ልብሱን እጠቢለት፤ ፈገግ ብለሽ ተቀበዪው፤ አብራችሁ ተዝናኑ፤ ከጎኑ አትለዪ፡፡ ታድያ ምግብ ስታቀርቢ፣ መጠጥ ስትሰጭው ከዚህ መድኃኒት ትንሽ ብትን አድርጊበት፡፡ ስትተኙም አልጋው ላይ በግርጌው በኩል በተን አድርጊ፡፡ ልብስ ስታጥቢም ይህንን ጨምረሽ አብረሽ እጠቢበት፡፡ በየጊዜው ቤቱን በሚገባ አዘጋጅተሽ በየጥጋ ጥጉ ይህንን በተን በተን አድርጊ፡፡ ከዚያ የፈለግሺው ሁሉ ይሳካል» አላት ዐዋቂው፡፡
በቦርሳዋ የያዘቺውን ሁሉ ገንዘብ ሠፍራ ልትሰጠው ስትል፡፡ «የምትከፍዪው ባልሽ ከሞተ በኋላ ነው» አላት፡፡ ብታደርግ ብትሠራው ሊቀበላት አልቻለም፡፡ መድኃኒቷን ይዛ የሚሆነውን ሁሉ እያሰላሰለች ወጣች፡፡ ልትወጣ ስትል እንዲህ አላት «ባልሽ ጠባዩን መቀየር ይጀምራል፤ ያን ጊዜ መድኃኒቱ እየሠራ መሆኑን በዚህ ታውቂያለሽ»
ቤት እንደገባች ዐዋቂው ባዘዛት መሠረት ቤቷን ታዘጋጅ ጀመር፡፡ ያንን አይታው የማታውቀውን ጓዳ ጎድጓዳ መልክ መልከ ሰጠቺው፡፡ አቧራውን አራገፈች፤ ዕቃውን ቀየረች፤ ወንበር እና ጠረጲዛውን መልክ መልክ ሰጠቺው፤ ግድግዳው ታጠበ፤ አዳዲስ የጌጥ ዕቃዎች በየመልካቸው ተሰቀሉበት፡፡ ከዚያም ወደ ማዕድ ቤት ገብታ እጅ የሚያሰቆረጥም ዶሮ ሠራች፡፡ መጠጡ ተገዛ፤ ቡናው ተፈላ፤ ፈንዲሻው ተፈነደሸ፤ ቤቱ ዓመት በዓል መሰለ፡፡ ሁሉም ነገር ላይ ግን መድኃኒቱ በተን ተደርጓል፡፡
ባል እንደ ለመደው አምሽቶ ከሥራ ገባ፡፡ ዐዋቂው እንዳለው ለሚስቱ ስጦታ የሚሆን ሽቱ፣ ጫማ እና አበባ ይዟል፡፡ መንገድ ላይ ከመድኃኒቱ በተን አደረገበት፡፡ ምን እንደሚፈጠር ባለማወቁ ሲፈራ ሲቸር በሩን መታ፡፡ ድሮ «ምን ትደበድባለህ ከፍተህ አትገባም» የሚለው ድምፅ ነበር የሚሰማው፡፡ አሁን አንድ እጅ ከፈተለት፡፡ ቤቱ ፏ ብሏል፡፡ «ማርዬ ደኅና አመሸሽልኝ» ሲላት ልቧ ወከክ አለ፡፡ «መድኃኒቱ መሥራት ጀመረ ማለት ነው» አለች በልቧ፡፡ እቅፍ አድርጋ ሳመቺው፡፡ ዓይኑንም ጉንጩንም አላመነውም፡፡ ከመጠራጠሩ የተነሣ «እርሷ ናት የሳመቺኝ ወይስ እኔ ነኝ የሳምኳት» እያለ ይጠይቅ ነበር፡፡ ያ ዐዋቂ ያለው እውነቱን ነው ማለት ነው፡፡
ያመጣላትን ሰጦታ ስታይ «በውኔ ነው ወይስ በሕልሜ፣ ወይስ በቴሌቭዥን» አለች፡፡ «የኔ ፍቅር፣ በጣም ነው የምወድህ» አለቺና ወደ ወንበሩ ወሰደቺው፡፡ አብረው ተቀመጡ፡፡ እርሷ ምግብ ልታቀራርብ ወደ ጓዳ ስትገባ በፍጥነት ጎንበስ አለና ወንበሩ ውስጥ መድኃኒቱን በተን አደረገው፡፡
ምግቡን አቅርባ መጠጡን ልታመጣ ሄደች፡፡ አሁንም አወጣና ወጡ ውስጥ በተን አደረገ፡፡
እንደ ጉድ ተበላ፡፡ ተጠጣ፡፡ ከተጋቡ ከሁለት ወር በኋላ ጀምሮ እንዲህ እየተጎራረሱ በፍቅር በልተው አያውቁም፡፡ በሞቴ፣ አፈር ስሆን፣ እየተባባሉ ጨረሱት፡፡ መድኃኒቱ ሠርቷል አሉ በልባቸው፡፡ አምስት ዓመት ሙሉ ያልተጫወቱትን ወሬ ሲያወጉት አመሹ፡፡ አምሽተውም አልቀሩ ወደ እልፍኛቸው ገቡ፡፡ እርሷ ቀድማ ባኞ ቤት ገባች፡፡ እርሱ ተሽቀዳድሞ በራስጌ በኩል መድኃኒቱን በተን አደረገው፡፡ መጣች፡፡ ደግሞ እርሱ በተራው ባኞ ቤት ገባ፡፡ እርሷም በግርጌው በተን አደረገች፡፡ ሁሉም በተኑ፡፡ እነርሱም በፍቅር ብትን አሉ፡፡
ሌሊቱ የፍቅር ሆኖ አለፈ፡፡ ሁሉም በየልባቸው በመድኃኒቱ መሥራት ተደሰቱ፡፡ የሟችን ቀን መቼ እንደሚሆን መገመትም ያዙ፡፡
ያ ሕይወት ቀጠለ፡፡ መገባበዝ ነው፡፡ መዝናናት ነው፡፡ መጨዋት ነው፡፡ መደዋወል ነው፡፡ መነፋፈቅ ነው፡፡ አብሮ መውጣት ነው፡፡ አብሮ መግባት ነው፡፡ ያቺ የጠፋቺው «ዬ» ተመልሳ ገባች፡፡ እርሷም እነ «ዋ»ን ይዛ መጣች፡፡ «ዋ»ም «የኔ ቆንጆ፣ የኔ እመቤት፣ የኔ ጌታ፣ የኔ ማር» የሚባሉ ዘር ማንዘሮቿን ጋበዘቻቸው፡፡ እናም ቤቱ ሞቀ፡፡
አንዳንድ ጊዜ ረስተውት የልብ የልባቸውን ያወሩ ጀመር፡፡ ለምን እንደዚያ ሊሆኑ እንደቻሉ፡፡ መደማማጥ እና መስማማት ለምን እንዳቃታቸው ያወራሉ፡፡ ወዲያው ትዝ ሲላቸው ደግሞ በየግላቸው ተደብቀው መድኃኒቷን በተን ያደርጋሉ፡፡
እየቆዩ ይኼኛው ኑሯቸው እየጣፈጣቸው መጣ፡፡ የማይጠገብ ሆነባቸው፡፡ ተገናኝተው ለመለያየት ሲጨነቁ፤ ተለያይተው ለመገናኘት ሲነፋፈቁ ጊዜ አንድ ነገር አሳሰባቸው፡፡ የቤታቸው ሙቀት ሲጨምር፣ የልባቸው ትርታ ሲንር ጊዜ አንድ ነገር አሳሰባቸው፡፡ አንዱ ለአንዱ ታዛዥ፣ አንዱ ለአንዱ አሳቢ፣ አንዱ ለአንዱ አዛኝ፣ አንዱ ለአንዱ መካሪ ሲሆኑ ጊዜ አንድ ነገር አሳሰባቸው፡፡
ሁለቱም በየልባቸው፡፡ «ይህንን የመሰለ ኑሮ ለምጄ አሁን ቢሞትብኝስ/ ብትሞትብኝስ» ይሉ ጀመር፡፡ ሞት እንዳልናፈቃቸው፣ ሕይወት አጓጓቸው፡፡ ትዳር ምን እዳ ነው እንዳላሉ፣ ፍቺ ምን እዳ ነው ብለው አዜሙ፡፡
እናም ሁለቱም መድኃኒት አድርገዋል፤ ሁለቱም፣ ለመግደል አሢረዋል፡፡ ግን እንዲህ የሚሆን አልመሰላቸውም፡፡ ደግሞ ይህንን ምሥጢር አንዱ የሌላውን አያውቅም፡፡ በዚህ የፍቅር ሞቅታ ውስጥ አንዱ ከሌላው ይህንን ቢሰማ ምን ይላል? እያሉ ተጨነቁ፡፡
ባል ሲከንፍ ወደ ዐዋቂው ቤት ገሠገሠ፡፡
እርሱም እያለቀሰ ተንበረከከ «ሚስቴን መልስልኝ፤ እፈልጋታለሁ መልስልኝ በፊት ከከፈልኩህ ሦስት እጥፍ እከፍልሃለሁ፤ ብቻ መልስልኝ፡፡ እኔ እንደዚህ መሆንዋን መች ዐወቅኩ» እጁን እንደ ሚማጸን ሰው አቅንቶ ለመነው፡፡
«በል» አለ ዐዋቂው፡፡ «ከባድ ነገር ነው የጠየቅከኝ፤ ተነሣና እዚያኛው ክፍል ግባ» አለው፡፡ ተነሥቶ ወደዚያኛው ክፍል ሲገባ ዓይኑን ማመን አልቻለም፡፡ ሚስቱ ተንበርክካለች፡፡ እንዴት መጣች? አለ በልቡ፡፡ ሮጦ ተጠመጠመባት፡፡ «ይቅር በይኝ የኔ ማር» አለ አቅፏት እያለቀሰ፡፡ «አንተ ይቅር በለኝ እንጂ» አለቺው እንዳቀፈቺው፡፡
«ቁጭ በሉ» አለ ዐዋቂው፡፡
ተቀመጡ፡፡
«ሁለታችሁም ባልኳችሁ መሠረት መድኃኒቱን አድርጋችኋል?» ሲላቸው ተያዩ፡፡ ተደናገጡ፡፡ «አንቺም አድርገሻል?» አለ ባል፡፡ «አንተም አድርገሃል?» አለች ሚስት፡፡ «አለቅና» ተባባሉ፡፡
«አላለቃችሁም» አለ ዐዋቂው፡፡ «የሰጠኋችሁ መርዝ አይደለም» ሲላቸው ዘለው ተቃቀፉ፡፡ «እንዲሁ ተራ ቅጠል ነው፡፡ የናንተ ችግር አለመተዋወቅ ነው፡፡ ውስጣችሁ ፍቅር አለ፡፡ ግን ፍቅራችሁን መግለጥ አልቻላችሁም፡፡ ለፍቅር እድል አልሰጣችሁትም፡፡ ትዳር ብዙ በመነጋገር እና በመወያየት ሳይሆን አንዳችሁ ለሌላችሁ በማድረግ ነው የሚገነባው፡፡ አንዱ ሌላው የሚፈልገውን ካደረገ፣ ራሱ የሚፈልገውን እንዳደረገ ይቆጠራል፡፡ ባል ለሚስት፣ ሚስትም ለባል መኖር አለባት፡፡ ባል ራሱን በሚስቱ ውስጥ፣ ሚስትም ራስዋን በባልዋ ውስጥ ማግኘት አለባት፡፡
ብዙ ባል እና ሚስቶች ለመዳር እንጂ ለመጋባት አልታደሉም፡፡ አብረው ይኖራሉ እንጂ አንዳቸው በሌላቸው ውስጥ አይኖሩም፡፡ ትዳር ማለት የሁለት ወንድ እና ሴት ወደ አንድ ጎጆ መግባት አይደለም፡፡ ባል ወደ ሚስት ሚስትም ወደ ባል ውስጥ መግባት እንጂ፡፡ ባል ራሱን ሚስቱ ውስጥ ካገኘው፡፡ ለሚስቱ የሚያደርገውን ለራሱ እንዳደረገው ነው የሚቆጥረው፡፡ ሚስትም እንዲሁ፡፡
ለወደፊቱም ብዙ አታውሩ፣ ግን ብዙ አድርጉ፤ አትዘዙ፣ ታዘዙ፤ እግዚአብሔር ሴትን ሰጥቶሃል፣ ሚስት ማድረግ ያንተ ድርሻ ነው፡፡ ለአንቺም እግዚአብሔር ወንድን ሰጥቶሻል ባል ማድረግም ያንቺ ድርሻ ነው፡፡
እንደ ተቃቀፉ ከዐዋቂው ቤት ወጡ፡፡ እነሆ ለትውስታ እንዲሆን ዛሬም ያንን መድኃኒት ትንሽ ብትን ያደርጋሉ፡፡
ከቨርጂንያ ወደ ላስ ቬጋስ ጉዞ ላይ፣ ዩናይትድ አየር መንገድ
ማስገንዘቢያ
የሃሳቡ መነሻ መንግሥቱ አሰበ የላከልኝ የቻይና ተረት ነው
Subscribe to:
Posts (Atom)