Friday, January 22, 2016

l#§êEnT MNDnW)

ክፍል ፩

l#§êEnT¼GlÖÆ§Yz@>N ”l# X.x.x 1944 jMé _QM §Y ynbr s!çN bMÈn@ hBT Mh#‰N zND k1981 jMé Xy¯§ ymÈ k1990ãc$ xU¥> jMé GN xh#N bBz#hN y¸ngrQN xYnTR GN²b@ bmÃZ |‰ §Y mêL yjmr xmlµkT nWÝÝ
19¾W X QDm 19¾W mè KFl zmN bx@Mp&¶Ãl!ZM nÚ yNGD  xStúsB §Y ytm\rt XNQS”s@ nbRÝÝ y‰s# mglÅãCM nb„TÝÝ Q" g™ãC _BQ yöÑlT YH £dT kFt¾ dr© mÃZ yjmrW xWé­êEÃN bx!ÇST¶ XÃdg# s!ÿÇ yQ" G²T ¥SÍÍT bjm„bT zmN nbRÝÝ  YHM G²TN bm-QlL½ `Y¥ñT ÆHL b¥SqyR½ yt¹ÂðWN wgN yx¹ÂðW wgN t‰ q$S xDR¯ bmG²T½ l¬§§Q yNGD yx!ÇST¶ tÌ¥èÒcW ?g(dNïCN ›lMxqÍêE mLK XNÄ!ñ‰cW b¥SgdD ytgli# nb„ÝÝbz!H £dT WS_ h#l# ¸²n# ytgßW kÄRêEÂêEW Xs@T ytgß ysW LíC yxÈ-R xStúsB nWÝÝ

bl@§ bk#L l#§êEnT ÆlûT mè ›m¬T BÒ y¬y úYçN ksW LíC UR ytö‰ß ¬¶K XNÄlW y¸ÃMn# xl#ÝÝ kz!H xNÉR l#§êEnT lBz# zmÂT ksWLíC mB²T½ k|LÈn@½ kXMnT ¥~b‰êE mStUBR½ xNÇ bxNÇ §Y lmqÄjT b¸ÃSbW yƧYnT Xn@ ÃLk#T x¥‰+ yl@lW mNgD nW wzt b¸l# ysWLíC -ÆY §Y ytm\rt YmS§LÝÝ  lz!HM XNdMúl@ ¥NúT y¸ÒlW bm6¾W mè KFlzmN yxrïC |LÈn@ yXSLM mSÍÍT £dTN½ ymñN¯L x!m­üR mSÍTN½ b16¾W 17¾W KFlzmN y±rt$UL ySp&yN yNGD mSÍÍT XSk x»¶µ mDrS ›lMxqÍêE q$R"TN½ b18¾W KFlzmN yx»¶µN NGD ›lMxqÍêEnT dr© mDrS wzT YH xYnt$ ;#dT Gn#"nT yöy lmçn# MLKT nWÝÝ
bMNfúêEW ysW LíC mStUBR SNmlkT dGä½ l#§êEnT k¦Y¥ñT ¥SÍÍT -Ɔ b§Y x!÷ñ¸ÃêE yNGD |‰ mLK Yø bGL} y¬yW b17¾W KFL zmN ydC x!NÄ!à ÷M­n! ymjm¶ÃW ›lMxqÍêE ÷R±Ê>N tBlÖ b¸¬wqW xKs!×N s!m\rT nWÝÝ YH ÷M­n! b›lM dr© ynbrWN yNGD ¥nöãCN xdUãCN l¥SwgD lmjm¶Ã g!z@ DNbR zlL yxKS×N ÷M­n! çñ bmÌÌÑ nWÝÝyxKs!×N ÷M­n!ãC dGä KFà bm¹_ xdU bmqnS byhg‰t$ µl#T tÌ¥T UR T||R bmF-R l#§êEnTN ÉMÄl#ÝÝ YH T||R bxƧT DRJèC bWS-# y¸z„ yyhg‰t$N ÆlÑÃãC ÆHL½ yyhg‰t$N ymNG|¬T DNUg@ãC b-Nµ‰ yxKs!×N KFà ƧcW xƧT F§¯T Xs@T UR l¥S¥¥T _rèC YdrUl#ÝÝ YHM ydµäc$N ¨ÆL hgéC ¥NnT b¥ÄkM wd-Nµéc$ y¥S-UT ¸Â tÅWaLÝÝ
xNÄNìC y19¾WN K.z. yx!÷ñ¸ l!B‰§Yz@>N ymjm¶ÃW l#§êEnT BlW Y-„¬LÝÝ bXnz!H sãC xmlµkT ›lMxqF NGD½ W+ gB q_t¾ x!Nv@ST»NT½ bxWé­ x!Mp&‰l!S¬êE `YlÖC Q" G²èÒcW §Y mNs‰ÍT½ XNÇh#M bx»¶µ yt-Âkr ymÈW yb§YnT nW Y§l#ÝÝbl@§ bk#L b2¾W ›lM õRnT xµÆb! kz!à b`§ çW l#§êEnT yNGD ZWWR w+ãCN y¸qNs# l!Ãq§_û b¸Cl# yt&Kñ©! W-@èC y¬gz s!çN lMúl@½UT/General Agreement on Tariffs and Trade/GATT/b¸ÆL ytlÆ yhg‰T yNGD Gn#"nT ¥s¶Ã WYYèC _§ SR nbRÝÝ  kz!ÃM k (1984 to 1995) btdrgW WYYT b;#‰UY §Y yhgéCN yNGD xlmGÆÆT y¸Ä" y›lM yNGD DRJT World Trade Organization (WTO) tm\rtÝÝ YH tÌM êÂW tGÆ„ ›lMxqF w_ yçn yNGD SRxT Gn#"nT XNÄ!ñR ¥mÒcT ¥SgdD nWÝÝ  kz!H b`§Â yh#lè×> kh#lT ybl-# hg‰T ywL xµÆb!ÃêE WlÖC tf-„ÝÝ lMúl@ yxWé­W y¥StcT WL½ ys»N x»¶µ ynÉ nGD ”- SMMnTNorth American Free Trade Agreement (NAFTA)/  X l@lÖCM yNGD XNQÍT y¸§*cWN y¬¶F ytlÆ bl#›§êE hgéC y¸drg# mk§kÃãCN h#l# ¥SwgD nWÝÝ
yl#§êEnT xYqÊnT xSf§g!nTN l¥SrÄT l@lÖC g#Ä×CM Ynúl#ÝÝ knz!H mµkL sW LJ bxND hgR xHg#R xNDnT BÒ l!k§k§cW wYNM l!Y²cW y¥YC§cW h#n@¬ãC  XNd DNbR zlL yW` yxyR BKlT¼pollution/½ ktf_é hBT xQM b§Y y›œÂ l@lÖC MRT ¥MrT xµÆN m¹R¹R¼natural environment y›lM ÑqT lW_½ y-fR x-”qM q$__R½ ›lM xqF x¹Æ¶nT mrB½ ›lMxqF ygNzB yNGD T||R wztN ÃqRÆl#ÝÝ
XNdmFTÿnTM xÄ!S ›lMxqÍêE TBBRN y¸ÃmÒc$ y¸Äß# tÌ¥TN kh#lt¾W ›lM õRnT wÄ!H ¥SÍÍT §Y Tk#rT bmS-T ytÆb„T mNG|¬T¼UN/ Â yBÊtNýDS tÌ¥TN¼Bretton Woods institutions/ X ›lMxqF yNGD DRJèC¼ multinational corporations /  X ›lMxqÍêE mLK çcW mNG|¬ê DRJèC¼global civil society/ mf-RNl#ÝÝ
Xz!H §Y åRèìKúêEÃN KRStEÃñC l!-Yq$T y¸gÆW _Ãq&½ Xnz!HN yt-qs#Tn ›lMxqÍêE ysW LíC h#l# yU‰ CGéC lmF¬T mtÆbR TBB„N bTGÆR CGR fcE l¥DrG ›lMxqF tÌ¥T mF-R xSf§g! l!çN YC§L¿ ngR GN ytÌ¥t$ m\rT y¸çnW y?G Xs@T ¥Sfi¸ÃW mNgD lKRSTÃÂêE x••R XNQÍT nW wYS dUð) µLçn yKRStEÃñC XRM© MN mçN xlbT) y¸L YçÂL Bü gM¬lh#ÝÝ

ይቀጥላል . . . .


Saturday, May 17, 2014

የንስሐ ጸሎት (በቅዱስ ኤፍሬም)

"ጌታዬ ሆይ! ይቅር በለኝ፤ ወደ አንተ በንስሐ እመለስ ዘንድም ብርታትን ስጠኝ፡፡ እንደ ቅዱስ ፈቃድህ በቅድስና እመላለስ ዘንድ ወደ አንተ መልሰኝ፡፡ የአጋንንት መኖሪያና ጎሬ የሆነውን ልቡናዬን እባክህ ቀድሰው፡፡
ጌታዬ ሆይ! እኔ ከአንተ ዘንድ ለራሴ ይቅርታን እጠይቅ ዘንድ የማይገባኝ ጎስቋላ ሰው ነኝ፡፡ በተደጋጋሚ ንስሐ ለመግባት ቃል እገባና ለራሴ የገባሁትን ቃል መጠበቅ ተስኖኝ ዋሾ ሆኜ እገኛለሁ፡፡ አንተ ከወደቅሁበት የኃጢአት አዘቅት በተደጋጋሚ ብታወጣኝም እኔ ግን በገዛ ፈቃዴ በደጋጋሚ በኃጢአት ተሰነካክዬ እወድቃለሁ፡፡ ስለዚህም ጌታዬ ሆይ! በራሴ ላይ እፈርዳለሁ፤ በመተላለፌ ከአንተ ዘንድ የሚመጣብኝን ቅጣት ሁሉ በጸጋ እቀበላለሁ፡፡ አምላኬ ሆይ! ስንቴ ጨለማ የወረሰውን ልቡናዬን በጸጋህ ብርሃንህ አበራኸው? እኔ ግን ተመልሼ ወደ ተናቀውና ከንቱ ወደሆነው አስተሳሰብ ተመለስሁ፡፡ ይህን ባሰብኩ ቁጥር ሰውነቴ በፍርሃት ይርዳል፡፡ ነገር ግን የኃጢአት ፈቃዴ አይሎ በኃጢአት አዘቅት ውስጥ በተደጋጋሚ እወድቃለሁ፡፡
ጌታ ሆይ ለእኔ ያሳየኸኝን የቸርነትህን ብዛት ዘርዝሬ ልጨርሰው እንዴት ይቻለኛል? እነዚህ ጸጋዎችህን ለእኔ ለማይገባኝ ሰው ሰጠሃቸው፤ ነገር ግን በስንፍናዬ በከንቱ አጠፋዋቸው፡፡ አንዳች ፍሬ ሳላፈራም ዘመኔን ጨረስኩት፡፡ አንተ በበረከቶችህ ሞላኸኝ እኔ ግን ለቸርነትህ አመፃን በብድራት መለስኩብህ ፡፡
ነገር ግን ጌታ ሆይ! እንደ ታጋሽነትህና እንደርኅራኄህ መጠን ፍሬ አፍርታ እንዳልተገኘችው የበለስ ዛፍ ለዘለዓለም ነቅለህ እንዳትጥለኝ እለምንሃለሁ፡፡ ለዘለዓለም ሕይወት የሚያበቃ ፍሬን ሳላፈራ በዘለዓለማዊ እሳት እንዳታጠፋኝ እማጸንሃለሁ፡፡ ጌታዬ ሆይ! ለፍርድ በመጣህ ጊዜ አንተን ለመቀበል ሳልዘጋጅ እንዳልገኝ ጠብቀኝ፡፡ ድንገት በመጣህ ጊዜ የዘይት ማሰሮዬ ሞልቶ መብራቴን ከዘይቴ ጋር ይዤ እገኝ ዘንድ እርዳኝ፡፡ የሰርግ ልብሴን ሳልለብስ በመገኘቴ ከሰርግህ ቤትህ ወደ ውጭ እንዳልጣል አድነኝ፡፡ አንተ ርኅሩኅ ጌታና ሰውን የምትወድድ ነህና ምህረትህ በእኔ ላይ ትብዛ፡፡ ጌታ ሆይ! ለፍርድ በመጣህ ጊዜ ነፍሴ በኃጢአት ተዳድፋና ከጸጋህ ተራቁታ እንዳትገኝ የንስሐ እድሜን ስጠኝ፡፡
ጌታ ሆይ! ጻድቅ በጭንቅ የሚድን ከሆነ የእኔ ከንቱና ኃጢአተኛ ሰው መጨረሻ ምን ይሆን? ወደ ሕይወት የምታደርሰው መንገድ ቀጭንና ጠባብ ከሆነች በቅምጥልነት የምኖረውና ለዓለማዊ ደስታ የምተጋው ሰው እጣ ፈንታዬ ምን ይሆን? ነገር ግን ጌታዬና መድኀኒቴ እንዲሁም ለእውነተኛ አምላክ እውነተኛው ልጁ የሆንክ ጌታዬ ክርስቶስ ሆይ! እንደ ፈቃድህና አንተ ለእኔ እንደምትመኛት ምኞት እንድኖር አብቃኝ፡፡ በአንተ ጸጋ ብቻ እንዳው በከንቱ በሰውነቴ ውስጥ ያደረውን የኃጢአት ፈቃድ አውጥተህ ጣልልኝ፡፡ ጌታዬ ሆይ እኔን ታድነኝ ዘንድ ፈቀድ፡፡ እጅግ ርኅሩኅና መሐሪ ለሆንከው ጌታ ምስጋና ይሁን ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን!

Wednesday, December 12, 2012

ዶሮና የሁለት ልጆች ፈተና


ምንጭ:-http://www.danielkibret.com

click here for pdf 
  ሁለት ተማሪዎች አንድ የቤት ሥራ ተሰጣቸው፡፡ የቤት ሥራው የተማሪዎችን ችሎታ ለመፈተን በከተማ ደረጃ የተዘጋጀ የዕውቀት መለኪያ ፈተና ነበር፡፡ ይህ ፈተና በሁለት ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች ተሰጥቷቸው ነበር፡፡ አንደኛው ተማሪ አባቱ የናጠጡ ነጋዴ ሲሆኑ እናቱም አሜሪካ ተወልደው አድገው በአንድ የውጭ ድርጅት ለመሥራት ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ናቸው፡፡ እርሱም የሚማረው ‹‹አበባ የቀጠፈና አማርኛ የተናገረ ይቀጣል›› የሚል ማስታወቂያ በተለጠፈበት አንድ የግል ትምህርት ቤት ነው፡፡ ሁለተኛው ተማሪ አባቱ የቀን ሥራ በመሥራት የሚተዳደሩ እናቱም ዶሮ የሚያረቡ ናቸው፡፡ ልጁም የሚማረው ከተቋቋመ ከሦስት ዓመቱ ጀምሮ መስኮቱ ተዘግቶ በማያውቅ አንድ የመንግሥት ትምህርት ቤት ውስጥ ነው፡፡

Monday, November 12, 2012

ከተራራው ጀርባ ያለው ሰው

ምንጭ:-http://www.danielkibret.com

እስኪ ታላቅ ነው በምንለው ቦታ ደርሰናል ብለን የምናስብ ሰዎች ለአፍታ ዘወር ብለን ተንጠላጥለንባቸው የተሻገርንባቸውን አያሌ ሰዎች ለማስታወስ እንሞክር፡፡ እዚህ ለመድረሳችን የምናውቀውንም የማናውቀውንም ድርሻ የተወጡ፣ እነርሱነታቸው እኛነታችን ውስጥ ያለ፡፡ አሁን የተቀመጥንበት ወንበር፣ የምንተኛበትም አልጋ፣ የምንኖርበትም ቤት፣ የምንቆጥረውም ብር፣ የወጣንበትም ከፍታ የእነርሱ ጭምር የሆነ፡፡ እነርሱ ባይኖሩ ኖሮ እዚህ ቦታ ለመድረስ ቀርቶ ወደዚህ አቅጣጫ እንኳን ለማየት የማይቻለን፡፡ እስኪ የሚቀጥለውን ታሪክ እየተከታተላችሁ እነዚህን አስቧቸው፡፡
መምህራን፣ የቤት ሠራተኞች፣ ሞግዚቶች፣ የሠፈር ሽማግሌዎች፣ አያት፣ አጎት፣ አክስት፣ የጥበቃ ሠራተኞች፣ ሾፌሮች፣ ጓደኞች፣ ሐኪሞች፣ ፖሊሶች፣ አንድ መሥሪያ ቤት ሄደን በጎ ያደረጉልን ሰዎች፣ ሳያስቡትም ሳናስበውም ዕድል የከፈቱልን ሰዎች፣ ሕይወታችንን የቀየረችውን አንዷን ብር የሰጡን ሰዎች፣ ከሞት ያተረፉን፣ ከመከራ የታደጉን ሰዎች፤ ያበረታቱን፣ ያጨበጨቡልን፣ የመረቁን፣ መንገድ ያሳዩን፣ በልብሳቸው አጊጠን፣ በምግባቸው ጠግበን እንድንጓዝ የረዱን፤ ከኛ በፊት ሕይወታቸውን ሰጥተው፣ ለኛ ሲሉ ተሠውተው ያለፉልን ጀግኖች፤ እነማን ነበሩ? እስኪ ይህንን ታሪክ እያነበባችሁ አስቧቸው፡፡

Friday, November 2, 2012

መንፈሳዊነት፦ ክፍል ፩

ምንጭ:-http://www.betedejene.org/


የሰው መንፈሳዊነት ከመንፈስ ቅዱስ ነው። ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን፦ “እነሆ እኔ የአባቴን ተስፋ ለእናንተ እልካለሁ (በነቢዩ በኢዩኤል የተነገረው ትንቢት ይፈጸምላችኋል) እናንተ ግን ከአርያም ኃይልን እስክትለብሱ በኢየሩሳሌም ከተማ ተቀመጡ።” ያላቸው ለዚህ ነው። ኢዩ. ፪፥፳፰-፴፪ ፣ ሉቃ ፳፬፥፵፱። እነርሱም ተስፋውን አምነው ለአሥር ቀናት ጸንተው በመቆየታቸው ለአሥሩ መንፈሳውያት ማዕረጋት የሚበቁበትንና በአሥሩ የመላእክት ከተሞች እንዳሉ ቅዱሳን መላእክት የሚተጉበትን ጸጋ በእሳትና በነፋስ አምሳል አግኝተዋል። የሐ ፪፥፩-፬።

Thursday, November 1, 2012

Wednesday, October 31, 2012

118ኛው ፓትርያርክ መንገድ ላይ ናቸው

 ምንጭ :-http://www.danielkibret.com/2012/10/118.html#more

ዐቃቤ መንበር አቡነ ጳኩሚስ ድምጽ ሲሰጡ
የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን 118ኛውን ፓትርያርክ የመምረጡ ሂደት ወደ መጨረሻው ምዕራፍ ተሻግሯል፡፡  በቤተ ክርስቲያኒቱ ሕግ መሠረት አዲስ ፓትርያርክ ለመምረጥ አራት ሂደቶችን ማለፍ ያስፈልጋል፡፡ የጥቆማና ማጣራት፣ የመጨረሻዎቹን አምስት ዕጩዎች የመወሰን፣ ለዕጣ የሚቀርቡትን ሦስት አባቶችን መምረጥና የመጨረሻውን አባት በዕጣ መምረጥ ናቸው፡፡
በዚሁ መሠረት ከተጠቆሙት ወደ አሥራ ሰባት አባቶች መካከል የማጣራቱና አምስቱን የመወሰኑ ሂደት እጅግ ረዥም ጊዜ የወሰደ መሆኑ ታውቋል፡፡ ይህ ሂደት ሁለት ከባባድ ችግሮች ተጋርጠውበት ነበር፡፡ የመጀመርያው ፈተና በቤተ ክርስቲያኒቱ ቀኖና ከተጻፈውና የግብጽ ቤተ ክርስቲያንም ሕግ ከሚደነግገው ውጭ ሀገረ ስብከት ያላቸው አባቶች ራሳቸውን ሳይቀር ለዕጩነት መምረጣቸው፣ ከዚህ በፊት አንዳንድ ችግሮች ተከስተውባቸው የነበሩ አባቶችም በዕጩዎች ዝርዝር ውስጥ መግባታቸው ነበር፡፡
ይህ ሁኔታ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ቀኖናና ሕግ ጋር የሚጋጭ በመሆኑ ራሳቸውን ከዕጩነት እንዲያገልሉ በአስመራጭ ኮሚቴውና በቤተ ክርስቲያኒቱ ታላላቅ አባቶችና ሽማግሌዎች የማግባባትና የማረም ሥራ ሲሠራ ነበር፡፡ ለሁለት ጊዜ ያህል ሱባኤ ታውጆ፣ ጳጳሳቱም ሁሉ ወደ አባ ብሶይ ገዳም ገብተው በጸሎትና በውይይት ችግሩን ለመፍታት ጥረት አድርገዋል፡፡ በዚህም ምክንያት የተወሰኑት አባቶች ‹እኔ በሺኖዳ መንበር መቀመጥ የለብኝም› እያሉ ራሳቸውን ከዕጩነት አግልለዋል፡፡ 
ከዚያ በኋላም ቢሆን የዕጩዎቹ ቁጥር በመብዛቱና በምእመናኑም ዘንድ በአንዳንድ ዕጩዎች ላይ ቅሬታ በመፈጠሩ የምርጫ ኮሚቴው ጊዜ ወስዶ ችግሮቹን ለመፍታት ሞክሯል፡፡ እጅግ የባሰው ሁለተኛውም ፈተና የተጀመረው በዚህ ጊዜ ነበር፡፡
አንዳንድ ዕጩዎች በቴሌቭዥን ፕሮግራም ሳይቀር ልክ እንደ ፖለቲካ ተመራጮች የምረጡኝ ዘመቻ ጀመሩ፡፡ ሕዝቡ ግራ ተጋባ፡፡ ዐቃቤ መንበሩ አባ ጳኩሚስ አንዳንድ ክርስቲያን የቴሌቭዥን ጣቢያዎችን እስከ ማስጠንቀቅ ደረሱ፡፡ በዚህ ጊዜ ምእመናኑና አባቶች በወሰዱት ቆራጥ አቋምና ግፊት አንዳንድ እጩዎች ከዕጩነት እንዲወጡ ተደረገ፡፡ በመጨረሻም አምስት አባቶች ቀሩ፡፡ በዚህ ሂደትም አምስት ጳጳሳትና ሰባት መነኮሳት ከዕጩነት ወጡ፡፡ በሂደቱ ከዕጩነት ከወጡት መካከል የሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ አቡነ ቢሾይ፣ የቀድሞው ፓትርያርክ ረዳት የነበሩት አቡነ ቡትሮስና የመንበረ ፓትርያርኩ ዋና ጸሐፊ አቡነ ዮሐንስ ይገኙበታል፡፡ 
በግንቦት ወር የተጀመረው 118ኛውን ፓትርያርክ የመምረጡ ሂደት ባለፈው ሰኞ ወደ መጨረሻው ደረጃ ተሸጋግሯል፡፡ ሰኞ ዕለት በካይሮ አባስያ በሚገኘው የቅዱስ ማርቆስ ካቴድራል ከአምስቱ አባቶች ሦስቱን በድምጽ የመለየት ሂደት ተከናውኗል፡፡
የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ሕግ እንደሚፈቅደው ብቃት ያላቸው የሚባሉት ድምጽ ሰጭዎች ቁጥራቸው 2411 ነው፡፡ እነዚህ ድምጽ ሰጭዎች በቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር ሥር ያሉ ካህናት፣ የገዳማት ተወካዮች፣ የምእመናን ተወካዮች፣ በግብጽ ፓርላማ ወንበር ያላቸው የኮፕት ማኅበረሰብ ተወካዮች፣ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ተወካዮችና ክርስቲያና ጋዜጠኞችን ያካተተ ነው፡፡